አገር በቀሉ ኩባንያ 128 ሺሕ ሔክታር መሬት በማግኘት ቀዳሚ ሆነ

– በቀን 1000 ቶን ስኳር ለማምረት አቅዷል

በኃያል ዓለማየሁ

በ90 ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የተቋቋመው አምቦ ነመር አግሮ ኢንተግሬትድ ኤንድ ኢንዱስትሪስ አክሲዮን ማኅበር በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ 128,000 ሔክታር መሬት በማግኘት ቀዳሚ ኩባንያ ሆነ፡፡ ኩባንያው መሬቱን ያገኘው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሲሆን፣ የአዲስ አበባን ስድስት እጥፍ የሚሆን 300,000 ሔክታር የእርሻ መሬት ለማግኘት ከሚጠብቁ ጥቂት የውጭ ኢንቨስተሮች ተርታ አሰልፎታል፡፡

አምቦ ነመር በተከፈለ ሁለት ቢሊዮን ብርና በተፈቀደ ሁለት ቢሊዮን ብር ካፒትል መመሥረቱን የገለጹት የኩባንያው የቦርድ አባል አቶ ደረጀ ደጀኔ፣ ኩባንያው በቀን 1000 ቶን ስኳር ማምረት የሚያስችለውን ፋብሪካና የሸንኮራ አገዳ ልማት ለማካሄድ እንዳሰበም ተናግረዋል፡፡

በግብርናና የግብርና ውጤቶች፣ በሲሚንቶና በግንባታ ዕቃዎች፣ በማዕድናት፣ በኢንዱስትሪ ውጤቶችና በንግድ ፕሮጀክቶች በከፋፈላቸው አምስት ዘርፎች የሚሰማራው ይህ ኩባንያ፣ ምርቶቹን ለአገርና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብም አቶ ደረጀ ገልጸዋል፡፡

በፍራፍሬና በአትክልት፣ በምግብ ዘይትና በሌሎች የግብርና ውጤቶች ከመሰማራቱም ባሻገር በአግሮ ኢንዱስትሪ ተሳትፎውም በእንስሳት እርባታ ሚናውን እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ የሰጐን፣ የዶሮና የአሣ ምርቶችን አቀነባብሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያለውን ዕቅድ አቶ ደረጀ አስረድተዋል፡፡

በቁም እንስሳት በኩልም በግና ፍየል በማርባት ትልቅ ቄራ መገንባትና የእንስሳት ውጤቶችን በማሸግ ጭምር ለውጭ ገበያ በማቅረብ ለማሳካት ያቀደው አምቦ ነመር፣ በተመረጡ የቡና ዓይነቶች ላይ በመሰማራት በርካታ ሥራዎችን እንደሚሠራ አቶ ደረጀ ይገልጻሉ፡፡

ኩባንያው ከ50,000 እስከ 100,000 ሕዝብ በማሳተፍ እስከ ሁለት ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ የሚያስችለውን የአክሲዮን ሽያጭ በዕቅዱ መሠረት ያቀረበ ሲሆን፣ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ይታሰባል፡፡

በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ አካባቢ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቦታ 128,000 ሔክታር መሬት ያገኘው ኩባንያ፣ የጉደር ወንዝን በመጥለፍ መሬቱን በመስኖ የማልማት ዕቅድ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

http://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article&id=4940:—128——&catid=98:2009-11-13-13-41-10&Itemid=617

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s